Quantcast
Channel: Oromia
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1918

#OromoProtests – Condemnation of Brutal Regime of Woyyaane continues

$
0
0

konso
በኮንሶ ግጭቱ አገረሸ ፤ ሰዎች ተገደሉ:: የካራት ከተማና አጎራባች ቀበሌዎች ትምህርት ቤቶች ተዘጉ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎KonsoProtests‬ ‪#‎SouthEthiopia‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Freedom‬ ‪#‎Konso‬
Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – በኮንሶ ህዝብ የተነሳውን የአከላለል ጥያቄ ተከትሎ በሕወሓት አገዛዝ ታጣቂ ኃይሎችና በህዝቡ መካከል የተነሳው ግጭት ላለፉት ሁለት ቀናት ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም እንደገና አገርሽቶ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ ሁለት ደግሞ ቆስለዋል፡፡ የካራት ከተማ አጎራባች ከሆኑት ቀበሌዎች አንዱ በሆነው ደበና ቀበሌ ወጣት ፋንታዬ ጊዮርጊስ፣ ወጣት ሞሎ ቱሌ እና አንድ ስሙ ያልደረሰን 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ሥራ አጥ ወጣት በሕወሓት አገዛዝ የጸጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሲሆን በተጨማሪም ሁለት ወጣቶች ቆስለዋል ፡፡ በዚህ ግጭት ሳቢያ የካራት ከተማና አጎራባች ቀበሌዎች እስካሁን ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ሲሆን ከተማዋና አካባቢው በመኪና ላይ በተጠመዱና የነፍስ ወከፍ መትረየስ ታጣቂዎች ተወሮ፣ ኮንሶ ልዩ ወረዳ ከዳር እስከ ዳር በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ናቸው፡፡
የኮንሶ ህዝብ የጀመረውን የአከላለል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በህዝቡ ላይ በደቡብ ልዩ ኃይልና መከላከያ ሰራዊት እየደረሰ ያለው የአፈና ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚሁ መሰረት በከተማው የሰፈረው ታጣቂ ከከተማዋ አጎራባች ቀበሌዎች እየዘመተ በህዝቡ የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት በሚል በዜጎች ላይ በሚወስደው የኃይል እርምጃ በ- ደቤና ቀበሌ ገ/ማ አቶ ‹‹ሷይታ ጋራ ›› ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ወጣት ‹‹ ተስፋዬ ማሙሽ›› ከ -ከርታሌ ቀበሌ እግሩ ተሰብሮ በባህል ህክምና እየተደረገለት በካራት ከተማ የሚገኝ ሲሆን አንድ የ65 ዓመት አዛውንትም ተሰብረው ባሻ ጤና ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ ከባለፈው ዓርብ/25-06-08/ ጀምሮ 23 ሰዎች/ሃያ ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት/ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው በከተማዋ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ተገልጧል፡፡ በከተማዋ የሚገኙት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ የተዘጉ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛው ወደ እስር ቤት ተቀይሯል፡፡
ወደከተማው የሚያስገቡ መንገዶች እስካሁን የተዘጉ ሲሆን በተለይ የ -ደራ እና ጃርሶ ቀበሌ ነዋሪዎች መትረየስ በታጠቁ የልዩ ኃይል አባላት ተወረዋል፡፡ በጃርሶ ቀበሌ ሰገን ወንዝ ዳር የሰፈረው ኃይል የነዋሪዎችን ፍዬሎች እየዘረፈ አርዶ እንደሚበላ፣ የፓፓያ፣ማንጎ አቮካዶ እና የፍራፍሬ ዛፎችን በበቀል ስሜት እያበላሸ/እያወደመ እንደሚገኝም ህዝቡ በምሬት እየገለጸ ነው፡፡
ታጣቂ ኅይሉ በዚህ የኃይል እርምጃ የካራትን ከተማ አቋርጦ የሚያልፈውን የአርባ ምንጭ -ጂንካ መንገድ ማስከፈት ቢችልም ከተማዋን ከማሳለፍ ውጪ የሚሰጠው ዋስትና ያለመኖሩ አሽከሪካሪዎችን ስጋት ላይ በመጣሉ ከመንግስት መኪናዎች ውጪ የትራንስፓርት እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ የመንግስት መኪና ተጠቃሚዎችም ቢሆኑ ከልዩ ኃይል ጋር ተነጋግረው መግባባት ባለመቻላቸው በትናንትናው ዕለት የደቡብ ኦሞ/ጂንካ ባለሥልጣናትን ይዞ ይጓዝ የነበረ መኪና ለ2 ሰዓታት ካራት ላይ በታጣቂ ኃይሎች ታግቶ ቆይቶ እንደተለቀቀ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ ከተማዋና አካባቢው በመኪና ላይ በተጠመዱና የነፍስ ወከፍ መትረየስ ታጣቂዎች ተወሮ፣ ኮንሶ ልዩ ወረዳ ከዳር እስከ ዳር በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል ፡፡ የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ፣ሴቶችና ህጻናት ሳይቀሩ ቱንም ዋጋ እንከፍላለን እንጂ ጥያቄኣችን ሳይመለስ ወደቤት አንገባም /አንመለስም በማለት ያላቸውን ቁርጠኝነት እየገለጹ መሆኑን እነዚሁ ታማኝ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ እኛም የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ሆይ ‹‹አፈና እና የኃይል እርምጃ ›› የህዝብን ብሶት ሲባብስ እንጂ ለህዝብ ጥያቄ መልስ አይሆንምና ከህዝቡ ላይ እጅህን አንሳ፣ ለሰላማዊ ጥያቄው ተገቢውን ምላሽ ስጠው፣ ህገ መንግስታዊ መብቱን አክብርለት እንላለን ፡፡


Solidarity Rally in Pretoria @ department of foreign affairs of South Africa

freebekele


#OromoProtests – Still going strong. This young boy was on the focal in November and December 2015
pretorianowandthen
#OromoProtests – Global Solidarity, Michigan, March 11, 2016
michigan
michigan1

Viewing all articles
Browse latest Browse all 1918