Quantcast
Channel: Oromia
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1918

በኬንያ ናይሮቢ ኢትዮጵያ ኤምባሲ የወያኔ የደህንነት ኣባላት ሚስጥራዊ ስብሰባ ተደርገ

$
0
0

woyane_security

(Mereja) — በኬንያ የወያኔ ኤምባሲ ጽ\ቤት የሕወሓት ሰዎችንና በስደተኛው ውስጥ ገብተው የሚሰልሉ የወያኔ ደህንነት ኣባላትን ያካተተ ስብሰባ ተካሂዷል።በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ በጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ለደህነቶች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው ::

በትላንትናው እለት ማለትም ሐምሌ 13 ቀን 2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገው እና ሙሉ ቀን በፈጀው ሚስጥራዊ የደህንነት አባላት ስብሰባ በኬንያ እንዲሰሩ የተመደቡ የደህንነት አባላት ስራቸውን በአግባቡ እየተወጡ ባለመሆኑ በስራ ላይ መዝረክረክ እያሳዩ በመሆን እና ክትትሉ በመላላቱ ናይሮቢን መናህሪያቸው ያደረጉ ጋዜጠኞች እና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የመንግስትን እና የሀገሪቱን ገፅታ ለማበላሸት ከአለማቀፍ ተቅዋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ከመሆኑም ባሻገር በሀገር ውስጥ የሚደረጉ እና ጸረ ሰላም ሀይሎች የሚፈጥሩዋቸውን እና እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴዎች በማጋጋል እና የመረጃ ልውውጦችን እያደረጉ ሀገሪቱ ወደማያባራ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ እያደረጉ በመሆኑ በአስቸኩዋይ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚል መመሪያ መተላለፉን ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ በስብሰባው ላይ ተካፋይ የነበሩ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡እንደምንጮቻችን ገለፃ የመጀመሪያው ትኩረት እንዲደረግባቸው ተብሎ ከተቀመጡት በቅርቡ በሌለበት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ የተወሰነበት ጋዜጠኛ ግዛው እና በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ርሃብ አድማ ያደረጉ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከስብሰባው ተሳታፊዎች የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ከኢትዮጵያ ሸሽተው የመጡ ፓለቲከኛና ጋዜጠኞች በነፃነት በኬንያ ውስጥ ተደራጅተውና ማህበር መስርተው ሲንቀሳቀሱ የተሰጣችሁን ተልኮ አልፈፀማችሁም በማለት በናይሮቢ የሚገኙ የወያኔ ሰላዮች በኣለቆቻቸው ተወቅሰዋል። የተሰጣችሁን ተልእኮ በተግባር ኣልተወጣችሁም በማለት ከፍተኛ ቁጣ ወርዶባቸዋል::

በተጨማሪ በኬንያ ናይሮቢ የሚኖሩ ስደተኞች አምስቲ ኢንተርናሽናል የርሃብ አድማ በማለትና የሀገሪቱን የፓለቲካ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በማህበራዊ ድህረገጾች ንቁ ተሳታፊ ሆነው ተቃዋሚ ስደተኞች ሲጠናከሩ ሰላዮቹ ፈዘዋል በሚል ተወርፈዋል። የግለሰቦችን ስም እየጠቀሱ መፍትሄ ያሉትን ሲመክሩና ሲወያዬ መዋላቸውን ምንጮች ገልፀዋል የእያንዳንዱ ተቃዋሚ ስደተኛ ኣዋውል እና እንቅስቃሲ እንዲጠና በተለይ ጋዜጠኛ ግዛውን የወያኔ ሰላዮችና ተላላኪዋች ክትትል አንዲያደርጉበት ያለበትን ቦታ ጥናት ማድረግ እንዳለባቸውና ቀጣይ ከዚህ በኋላ ወደ ስራ እንዲገቡ የስራ መመሪያ እንደተላለፈላቸው በስብሰባው ላይ ከተሳተፉ ምንጮች ለመረዳት ተችሏል።


በሰንዳፋ ያሉ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች የአዲስ አበባ ቆሻሻ ከዚህ በኋላ እንዳይመጣብን ሲሉ ከለከሉ።

በአዲስ አበባ ካለፈው ሣምንት ጀምሮ ለ7 ቀናት በዋና ዋና የከተማዋ አውራ ጎዳናዎች፣ መንደሮች እንዲሁም ገንዳዎች ቆሻሻ ተከማችቶ ሰንብቷል…

የቆሻሻ ማንሻ መኪኖች የተሸከሙትን ቆሻሻ የሚያራግፉበት አጥተው ቆመዋል፡፡

ለወትሮው የከተማዋን ደረቅ ቆሻሻ ሸክፈው ሰንዳፋ ወደሚገኘው ዘመናዊ የቆሻሻ መጣያ ቦታ መሄድ የነበረባቸው እነዚሁ መኪኖች ወደ ሰንዳፋ ማቅናት አልሆነላቸውም፡፡

ሸገር የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት አቶ ዳዊት አየለ ጋር ስለ ሰሞኑ የፅዳት ችግር ተነጋግሯል፡፡

አቶ ዳዊት ከመኖሪያ ቤትና ድርጅቶች ከሌሎችም ተቋማት የተሰበሰበው ቆሻሻ በወጉ ሊወገድ አለመቻሉን ተናግረው የቆሻሻ ክምር ወደ ሰንዳፋ ወስዶ ለመጣል ጊዜያዊ የተባለ ችግር ተፈጥሯል፡፡

13710058_10155067053364616_884587906856021924_nበሰንዳፋ ያሉ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች የአዲስ አበባ ቆሻሻ ከዚህ በኋላ እንዳይመጣብን ሲሉ መከልከላቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ የየዕለት ደረቅ ቆሻሻ እየተረከበ በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድ እንዲረዳ ተብሎ በሰንዳፋ የተገነባው የቆሻሻ መረከቢያ ማዕከል በዚህ ሰሞን አገልግሎቱን አቋርጧል፡፡

ከ7 ዓመት በፊት ይህ ማዕከል ስለሚሰጠው አገልግሎት መንግሥት ግልፅ ውይይት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ማድረጉንና ተቀባይነትንም እንዳገኘ የሚያስታውሱት አቶ ዳዊት የፅዳት አስተዳዳር ሥራ አስኪያጅ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በኋላ ቆሻሻው ሸቶናል መሠረተ ልማት ይሟላልንና ሌሎች ጥያቄዎች ማንሣት ጀምሯል ይላሉ፡፡

በሰንዳፋ ያለው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማዕከል ሥራ ከጀመረ መንፈቅ አልፎታል፡፡ በዚህ ሣምንት ግን ቆሻሻውን መረከብ በማቆሙ ምክንያት ከተማዋ ቆሽሻ ሰንብታለች፡፡

የአዲስ አበባን ቆሻሻ ለረዥም ዘመናት ሲቀበል የከረመው ረጲ ተመልሶ እንዳይከፈት ሆኖ ተዘግቷል የሚሉት አቶ ዳዊት የከተማዋን ቆሻሻ በማስተናገድ በኩል የ50 እና የ60 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጥ የተዘጋጀው የሰንዳፋ ማዕከል አሁን የተፈጠረበትን ጊዜያዊ ችግር ለመፍታት ኮሚቴ መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡

ኮሚቴው ትናንት ከሰንዳፋ አካባቢ ቅሬታ አቅራቢዎች ጋር ድርድር ማካሄዱንና የድርድሩ ውጤት ለጊዜው እንዳልሰመረ ሰምተናል፡፡

(ሕይወት ፍሬስብሃት)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1918