Quantcast
Channel: Oromia
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1918

#OromoProtests and ‪#‎GonderProtests‬, August 5, 2016

$
0
0





‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Amharaprotests‬ ‪#‎Goder‬ ጎንደር የሕዝብ ተቃውሞ ቀጥሏል ፡፡ አዘዞ ሙሉ ለሙሉ በወጣቱ ቁጥጥር ስር ወድቃለች። ህዝቡ በጣም በቁጣ እዬተንቀሳቀሰ ነው። የህወሓት አባል እና የሰላይ ንብረቶች ላይ እርምጃ እዬተወሰደ ነው። ዳሽን ቢራ ስፖንሰር ያደረጋቸው ሱቆች ወድመዋል። ‪#‎MinilikSalsawi‬
13880330_1759188597685669_2309007068093584446_n

‪#‎GonderProtests‬
13876348_622753101225763_6317602346769698296_n


#AddisAbaba #Demonstration የኣዲስ አበባ ወጣቶች ከዚህ ቀጥሎ የተመለከተውን መልዕክት የያዘ በራሪ ወረቀት በራሳቸው ተነሳሽነት አሳትመው እያሰራጩ ነው

ጉዳዩ: ሰላማዊ ሰልፍ ማወጅን ይመለከታል፡፡#Oromoprotests#Amharaprotests

በ25 አመታት የኢህአዴግ አገዛዝ ዉስጥ ከስርአቱ ተጠጊዎችና ከስርአቱ አቀንቃኞች ዉጪ አንድም የተጠቀመ ሰዉ እንደሌለ እሙን ነዉ፡፡”በመሆኑም ብሄራዊ ክብሬ ተነክቷል፤ ሰበአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቴ ተጥሷል፤ በሀገሬ ሰርቼ መኖር አልቻልኩም፤ ድግሪን የሚያህል የት/ርት ደረጃ ይዤ ድንጋይ እንድፈልጥ ነዉ የተፈረደብኝ፤ በአንጻሩ ምንም ያልተማረ ድልብ መሃይም ካድሬ ኢህአዴግን ስለተጠጋ ብቻ በአንድ ለሊት ባለጸጋ ለመሆን በቅቷል፤ እኔ ነጻነት አጥቻለሁ፤ ዴሞክራሲን በስሙ እንጂ አይቼዉም አላዉቅም፤ እኩልነት ምን እንደሆነ ብገነዘብም በኢህአዴግ አገዛዝ ዘመን ሲተገበር አላየሁም፤ ለራሳቸዉ ከቀረጥ ነጻ አስገብተዉ በቅናሽ ዋጋ ሲሸጡ እኔ ላይ ግብር ከምረዉ ከስራ ዉጪ ሆኛለሁ-ነግጄ ለመንግስት ነዉ ስሰራ የከረምኩት

ራሴን መለወጥ አልቻልኩም፤ መሬቴ በጉልበት ተወርሶብኛል፤ በሀገራቸዉ ስራ መስራት ባለመቻላቸዉ እህትና ወንድሞቼ ስራ ፍለጋ እንደወጡ በባህር ሰጥመዉ፤ በአሸባሪ ተገድለዉብኝ ልቤ ቆስሏል፤ እንደ እንስሳ እንጂ እንደ ሰው እየታየሁ አይደለም፤ ሁለተኛ ዜጋ እንደሆንኩ ነዉ የሚሰማኝ፤ ቤቴ ፈርሶ ሜዳ ላይ ተጥያለሁ፤ ቤታችን ለምን ይፈርሳል ብለዉ የተቃወሙ የቤተሰብ አባላቶቼ እስር ቤት ናቸዉ፣ በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ከመስሪያ ቤቴ ተባርሬአለሁ፣ ንብረት ለማፍራት ምንም ዋስትና የለኝም፤

ሀገሬን ባለግዜዎች ነጥቀዉኛል፣አማራ በመሆኔ ትምክህተኛ መርዝ ለሃጫም፣ ኦሮሞ በመሆኔ ጠባብ ዘረኛ ተብዬ ተሰድቤአለሁ የዘር ግንዴ ተሰልቶ አድልኦ ተደርጎብኛል፤ በኑሮ ዉድነት ምክንያት እንኳን ለመኖር ኑሮን ራሱ ሳስብ የተፈጠርኩበትን ቀን እርግማለሁ ይሄንንም የፈጠረዉ የመንግስት የቢሮክራሲ አሰራር እንደሆነ ቢገባኝም ፈርቼ ወይም ብቻዬን ሆኜ እስከ ዛሬ ታግዣለሁ፣ ፍርድ ቤት፣ የመከላከያ ሰራዊት፤ ፖሊስ የአንድ ድርጅት ዙፋን ጠባቂ እንጂ ነጻ ተቋማት ሆነው የህዝብ ወገኝተኝነታቸውን በግዢው ፓርቲ ተነጥቀዋል።

የምትል በሙሉ ቅዳሜ ሐምሌ 30/2008 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ መስቀል አደባባይ እንገናኝ፡፡ ክልል ላይ የምትኖር ከሆነ ደግሞ ወደ አንዱ የኦሮሚያ ክልል ወረዳና ዞን ጎራ በል በዕለቱ ህዝቡ ብሶቱን ያሰማል።
ድል የህዝብ ነዉ፡፡”

13729111_1759063144364881_1408782428944027497_n


‪#‎oromoprotests‬ Haala kanaan itti qophofte Qeerroon Aanaa daandii (Giincii dha)

13934913_622494964584910_3768876773312279153_n

13920837_1756991624578225_7045261297872081470_n


 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1918