#OromoProtests– Mormii Guddicha Oromiyaa keessatti Hagayya 6 bara 2016 gaggeeffamee ooleen lubbuun Oromoota wareegamanii 55 ol dhaqqabee jira. Wareegamtooti kunneen maqaan isaanii ammatti nu gahuu baatus, namooti addaddaa lakkoofsaa wareegamtootaa akkanatti gabaasaa jiru.
1. Asaasaa -13
2. Aawwadaay-8
3. Dodolaa- 5
4. Addeelee(H-B)-4
5. Haramaayaa-5
6. Amboo-4
7. Naqamtee-4
8. Mandii-2
9. Eddoo-2
10. Gimbii-1
11. Shaashamannee-1
12. Hirna-1
13. Qilxu Kaarraa-1
Mee maqaa wareegamtootaa warri beektan akka gabaasa waliigalaaf tolutti nuuf ergaa; Galatoomaa!!
Qaaman isinirraa fagaannus yaadafi Deeggarsa barbaachisun isin ciina jirra jedhu Oromoonni Magaala Jidda Saudi Arabia irraa. Qophiin kun wanta natti toleen keessaa tokkumman jarmiyoota akka mirkanaa’uf fedhiin miseensota jaraa olaanadha.
#FXG ሚናህን ለይ ። ይህ መልዕክት ከኦሮሞ እህት ፥ አባት፥ እናት ፥ ወንድምና ኦሮሞ ሕዝብ ወገንህ የተላከ መልዕክት ኦሮሞ ሆነህ በዚህ ጮቋኙና ጠባብ ቡድን ውስጥ የሚትሠራ ማንኛውም ሠራዊት ከወገንህ ቄሮና ኦነግ ሠራዊት ጋር ተቀላቀል ። የወቅቱ ጥሪ አሁን ነው ።
ጊዜ የሚሠጥ አይደለም ።
#OromoProtests Qabsoon Oromoo hanga bilisummaatti!
===============
”Oduu Amma nu gahe !!!
Godina Arsii Bahaa Aanaa munessa magaala Qarsaa Keeysatii Guyyaa hardhas mormiin cimaan gegeeyfamaara.
Mormiin guyyaa Hardhaa kan kaleeysaa irra caala jabaadha. Dalansuun hawaasa kalatii hundaan jabaata deemara. Adaduma dhiignii jiguun dhiignii danfa”.
Baalee Roobeetti Yeroo Ammaa Kana Lolli hamaan Akka Deemaa jirutu himamaa Jira. Qabeenyi wayyaanee Hedduun Akka barbadaa’es himamaa jira. akkasumas Ummanni lakkoofsaan hangana hin jedhamne ukkaamfamee Tana buuten isaanii dhabamtee Jirti
Oduu wal fakkaatuun Achuma godina baalee Magaalaa Dalloo Mannaatti namoonni baayyeen Rasaasaan Rukutamanii Akka hospitaala jiran himamaati Jira, Wayyaaneen Ummata mana yaalaa Nama rasaasaan dhawame Laaluuf dhaqan irrattis rasaasa bantee Jirti,
Via #Shamshadiin Caalanqo
#ሰበርዜና– በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ አራት አገራቶች ቻይና፣ግሪክ፣ጀርመንና ጃፓን ሲያወግዙት ሩሲያ በበኩሏ ለ እስራኤል መንግስት አፋጣኝ ደብዳቤ ልካለች “እናንተ በምትሰጡት መሳሪያ ብዙ ህዝብ እየሞተ ነው” ባፋጣኝ እስራኤል ለኢትዮጵያ መንግስት የምትሰጠውን የጦር መሳሪያ ማቆም እንዳለባት ስታሳስብ ሩሲያ ለግንቦት 7 ና ለሌሎች ድርጅቶች መሳሪያ ማስተላለፍ እንደምትጀምር አሳውቃለች ። ለበለጥመረጃ
==================================================
Breaking News – Ethiopian people on the murder of the four countries, China, Greece, Japan, Germany and Russia šiyewegizuti part, the government sent an urgent letter to Israel’s happening, “You bear a great tool for people dying is” bad Russia calls for Israel to stop the Ethiopian government šitešešibi your weapons and 7 others organizations already begin to transfer device. lebelet’imereje
#OromoProtests “Ergaa kibba Lixa shawaa anaa qarsaaf maallimaa magaala Lemman sadeen soddorraa nuuf dhufe:
Guyyaa kalesssaa 8 /6/2016 hiriira nagaa uummannii fi barattoonni hedduun karaa nagaatiin baanee galleerra haa tahu malee agaazii sa’aa booda magaala keenya galchisiisuun halkan tokkotti haga manni hidhaa guututti ol nu naqaa jiran.uummanni magaala leemman suuqii cufuun,hoteelota cufuun ,gabaa guddaa leemman mufannaa uummataatiin hiriirri bifa kanatti jijjiramee jira.Haa tahu malee hoteelota hamma kanaa osoo cufaa jiran hoteelli obbo Bulloo (Maallimaa Hoteel) kan jedhamu banuun Agaazotaaf nyaataa fi dhugaatii dhiyeessuun uummata keenya ficcisiisaa jira.seenaan boru akka isa gaafachuu dandahu uummanni leemman beeksisee jira.hoteela isaatiifis maqaa Maallimaa kennuun isaa hedduu nu qaanesseera.nuti uummanni qarsaa maallimaa namicha kanaaf obsa fixachaa jiraachuu keenya ibsuu barbaanna! Hojjottoonni OPDO aanaa qarsaa maallimaallee hedduu itti mufatanii jira.inni Agaazii waliin Cooma nyaachaa ,nuhimmoo Taffiin nu nyaachaa jiraachuun waan hin yaadamne” via Daraaraa Sabaa
በጠገዴ፣ አርማጭሆና ወልቃይት አካባቢዎች ውጥረቱ አይሏል፡፡ በሁለት ቀናት ብቻ የሞቱ ዐማሮች ቁጥር ከ65 በላይ ደርሷል:: #Ethiopia #AmharaResistance, #የአማራ_ተጋድሎ #Welkait
የዐማራ ተጋድሎ ውሎ ዘገባ ( ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም.) – ጠገዴ (ቅራቅር)፡ የተከፈተባቸውን ጦርነት በመፍራት ዐማሮች ሴቶቻቸውን እና ሕጻናቶቻቸውን እያሸሹ ነው፤ ዛሬ በቅራቅር የተጋድሎ ሰልፍ ተካሒዷልበጠገዴ፣ አርማጭሆና ወልቃይት አካባቢዎች ውጥረቱ አይሏል፡፡ የመከላከያ ሠራዊት በኹመራ በኩል ገብቶ በሶረቃና በማይደሌ አካባቢዎች በዐማሮች ላይ ይፋ ጦርነት ለማድረግ መዘጋጀቱን ነው ከቦታው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡ ከትግራይ ክልል ወደ አዲረመጥ ከተማ በአውቶቡስ ገብተው እኛ ትግሬዎች ነን በማለት ሰልፍ ለማድረግ የተደረገው እንቅስቃሴ እስካሁን እንዳልተሳካ ከጠገዴ አካባቢ ያሉ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በማይደሌና በቅራቅር አካባቢዎች ሁለት ኃይል ጦር ከነመካናይዝድ ትጥቁ መሽጓል፡፡ ባካባቢው ያገኘናቸው ምንጭች እንደሚጠቁሙት የወያኔ መንግሥት የግንቦት 7 አሸባሪ ገብቷል የሚል ሰበብ በመፍጠር በጅምላ ዐማሮች ላይ ጦርነት ሊታወጅ መሆኑን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን አገዛዙ በዚህ ምክንያት በቤተሰቦቻቸው ላይ የሚደርሰውን እልቂት ለመቀነስ በሚል ሴቶቻቸውንና ሕጻናት ልጆቻቸውን ወደ ጎንደርና ሌሎች አካባቢዎች እያሸሹ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ዐማራን ለመጨረስ ምክንያት እየተፈጠረ እንደሆነ የሚገልጹት ምንጮቻችን ይህ ሆን ተብሎ የተቀናበረውን ሴራ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና እንዲያደርግ ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ዛሬ በቅራቅር ከተማ ከመላው ጠገዴ የተመጡ ዐማሮች የተጋድሎ ሰልፍ አካሒደዋል፡፡ መጠኑ ከሃያ ሺህ በላይ የሚሆነው የተጋድሎ ተሳታፊ ወልቃይት ጠገዴን የዐማራ ማንነት ጥያቄ ለማዳፍ የሚደረገው ጥረት ሁሉ እንደማይሳካ ሲገልጽ ውሏል፡፡ ስልክና ኢንተርኔትን ጨምሮ ማንኛውም ዓይነት የግንኙነት ዘዴ ሁሉ ተቋርጧል፡፡ ከኹመራ ጎንደር መንገድ አግልሎት መሥጠት ካቆመ ቀናት ተቆጥረዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ዳባት፡ ወደ ወገራ አውራጃ ዳባት ስልክ ደውለን ነበር፡፡ በጠዋት የተጀመው ተጋድሎ ብዙም የተሳካ አልነበርም ብለዋል፡፡ ነገር ግን በስልክ ያነጋገርናቸው አንድ አዛውንት ተቆጥተው ‹‹ለመሆኑ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ›› አሉን፡፡ በዝርዝር ብንነግራቸውም ሊያምኑን አልቻሉም፡፡ ግን ‹‹አንተ ከየትኛውም ወገን ልትሆን ትችላለህ፤ ትሰማለህ ልጄ›› አሉና ቀጠሉ ‹‹መንግሥቱ የአንድ ክልል መንግሥት መሆኑን በተግባር አስመስክሯል፤ ዐማራው መኖር አልቻለም፡፡ ዝም ብንልም ብንናገርም ዐማራውን ከመግደል አይቆሙም፤ እኔ ከእንግዲህ መኖር አልፈልግም፡፡ ልኑር ብልስ ማን ያስኖረኛል! እንዲህ ዓይነት መንግሥት በዘመኔ አይቼ አላውቅም፡፡ ልጄ ትሰማለህ! ዐማራው ዝም ሲል አሸባሪ ይሉታል፤ መብቱንም ሲጠይቅ ተመሳሳይ ነው እና ምርጫ አጥተናል!!›› አሉኝ፡፡ ንዴትና የተጋደሎ ወኔ በአንድነት ከድምጻቸው ላይ ይነበብ ነበር፡፡
ሻውራ (አለፋ ጣቁሳ)፡ ትናንት ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. የአለፋ ጣቁሳ ሕዝብ በሻራ ከተማ የተጋድሎ ሰልፍ አድርጎ ነበር፡፡ የወያኔ አልሞ ተኳሽ ፌደራል ፖሊሶች በየቤቱ እየዞሩ 7 የሚሆኑ ዐማሮችን በጥይት ገድለዋል፡፡ ቁጥራቸው ያልታወቀ ዐማሮች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ በሻራ ከሞቱት አብዛኛዎቹ በየቤታቸው እንደሆነ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡
ጎንደር፤ የጎንደር ከተማ ዛሬ አንጻራዊ በሆነ መልኩ ሰላም ነበር፡፡ የማኅበረሰቡ እንቅስቃሴ ያን ያክል አልነበረም፡፡ መንገዶች በድንጋይ ተዘጋግተው ይታዩ ነበር፡፡ ትናንት አዘዞን ጨምሮ የሞቱት ሰዎች ብዛት የታወቀው 8 ያክል እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡ ኮሎኔል ደመቀ ከእስር ቤት ወጥቷል የተባለውም ወሬ ያልተረጋገጠ ውሸት ሲሆን ዛሬ ከማረሚያ ቤት ሒደው ያገኙትን ሰዎች በስልክ አነጋግረናል፡፡ በጎንደር የሞቱ ሰዎችና የወያኔ ሠራዊት አባለት ቁጥር በውል ለማወቅ ቀናት ያስፈልጋሉ፡፡ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ከተማዋን ለቀው እየወጡም እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በደምቢያ ወረዳ ቆላ ድባ ከትናንቱ የተለየ ነገር እንደሌለም ታውቋል፡፡ ማክሰኝት ከተማ ትናንት ሁለት ወጣቶች መሰዋታቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡
አዲስ ዘመን (ሊቦ ከምከም)፡ በአዲስ ዘመን ከተማ ዐማሮች ዛሬ ለተጋድሎ ወጥተው ነበር፡፡ ሊቦ ከምከም እና ከእብናት (አምቦ ሜዳ) አካባቢ የተሰባሰቡ ዐማሮች ዐማራው ይከበር፤ ወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ነው የሚሉ በርካታ የተጋድሎ መፈክሮችን ይዘው ወጥተዋል፡፡ ዛሬ በተደረገው ሰልፍ አንድ ዐማራ ተሰውቷል፡፡ የሟቾች ቁጥር አራት ነው የሚሉ መረጃዎች ቢኖሩም ማረጋገጥ የቻልነው አንድ ሰው መሞቱን ነው፡፡
ወረታ (ፎገራ)፡ በፎገራ ወረዳ ዐማሮች ለተጋድሎ የወጡት ዛሬ ከሰአት በኋላ ነበር፡፡ የሥርዓቱ አገልጋይ ናቸው በተባሉ ግለሰቦች ንብረት ላይ አደጋ የደረሰ ሲሆን በወያኔ በተመለመሉ ባንዳ ሚሊሻዎች አራት ዐማሮች ሲገደሉ ሁለት ደግሞ ቆስለዋል፡፡ የዐማራ ፖሊስ ሕዝባዊነት አሳይቶ ነበር፡፡ በወረታና በአዲስ ዘመን የተጋድሎ አስተባባሪ ሰው ችግር እንደነበርም ለማወቅ ችለናል፡፡
ባሕር ዳር (ጎጃም)፡ በባሕር ዳር ዐማሮች ላይ የተወሰደው ጭፍጨፋ ብዙ ወጣቶችን አስቆጥቷል፡፡ በባሕር ዳር የተለያዩ የጤና መስጫ ተቋማት በአስከሬኖችና ቁስለኞች ተጨናንቀው ውለዋል፡፡ እስካሁን በደረስን መረጃ መሠረት በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ካዳቨር ክፍል ያለፉ 22 አስከረኖች ሲኖሩ ሦስት ያክል ደግሞ ሆስፒታል ሳይገቡ ቀጥታ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሔዱ ነው የተገለጸው፡፡ ስለሆነም በባሕር ዳር የታወቀ 25 ያክል ዐማራ ሲገደል ቁጥሩ ከ40 በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ከቦታው ያነጋገርናቸው አንዳንድ ሰዎች ተናግረዋል፡፡
ደብረ ታቦር እና ጋይንት፤ በደብረ ታቦርና በጋይንት ዛሬ የተለየ ነገር አልተስተዋለም፡፡ ሆኖም የአካባቢው ወጣቶች ቁጭት የሚበርድ አይደለም፡፡ በሁለቱም አካባቢዎች የሞቱ ሰዎች ብዛት ከስድስት እንደሚበልጥ ነው የተነገረው፡፡
ማጠቃለያ፤ በሁሉም ቦታዎች በስልክ ያገኘናቸው ግለሰቦች እንደሚገልጹት ለሰላማዊ ሰልፍ ጥይት ከሆነ መልሱ እራሳችን የመመከት ሥራ እንደሚሠሩ ነው የተናገሩት፡፡ በባሕር ዳር ወጣቶች ከእንግዲህ ሕግ አለ ብለው እንደማያስቡ ለዚህም ማንኛውንም ዓይነት መስዋትነት እንደሚከፍሉ የገለጹ ሲሆን በዓለሙ ሁሉ የተሰራጨው ዐማራ እገዛ እንዲያደርግላቸው አሳስበዋል፡፡ Muluken Tesfaw